የኢቫሱ ዋና አላማ ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት ነዉ፡፡ ይህንንም አላማ ከግብ ለማድረስ ኢቫሱ ልዩ ልዩ ስልቶችን የሚጠቀም ሲሆን አገልጋይ መሪዎችን ማብቃት ከስልቶቹ አንዱ ነዉ፡፡ ብሔራዊ የመሪዎች ጉባኤ በሃገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የተማሪ ህብረት መሪዎችን ለማስታጠቅ እና አቅጣጫ ለመስጠት የሚሰበሰብ ጉባኤ ሲሆን፤ ብሔራዊ የተልእኮ ጉባኤ ደግሞ የወንጌል ስራ በሰፊዉ ይሰራ ዘንድ በወንጌል ዙሪያ የሚሰሩ ልዩ ልዩ የተማሪ አስተማባሪዎችን (mobilizers) ለማስታጠቅና አቅጣጫ ለመስጠት የሚሰበሰብ ጉባኤ ነዉ፡፡